ህዝባዊ ተቃውሞዉ አዲስ አበባ ደረሰ BBN news February 12, 2018

Standard

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ አዲስ አበባ መድረሱ ታወቀ፡፡ የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በመሐል ከተማ በዛሬው ዕለት የስራ ማቆም አድማ እንደተካሄደባት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በሰፊው የተተገበረው የዛሬው አድማ፣ በዋና ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ሲተገበር ማየታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ እንደ እማኞቹ ገለጻ፤ በአዲስ አበባ ትልቁ የገበያ ስፍራ መርካቶ ውስጥ የንግድ መደብሮች ተዘጋግተው የዋሉ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም የታክሲ አገልግሎት ተቋርጦ ተስተውሏል፡፡ መርካቶ ጣና ገበያ በተባለው የገበያ ስፍራ የተለያዩ የንግድ መደብሮች ተዘጋግተው እንደነበር የጠቆሙት መረጃዎች፤ በዚሁ ስፍራ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ተሽከርካሪዎችም ስራ አቁመው መዋላቸውን መረጃዎቹ ያክላሉ፡፡

በመሐል ከተማዋ በተወሰነ መልኩ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ፣ ዳር ላይ በሚገኙት የአዲስ አበባ ከተሞች ግን በሰፊው ተተግብሮ መዋሉን መረጃዎች አስታውቀዋል፡፡ በዓለም-ገና፣ ካራቆሬ፣ አየር ጤና፣ ጆሞ፣ ሰበታ እና በሌሎች አካባቢዎችም የስራ ማቆም አድማ የተደረገ ሲሆን፤ በተጠቀሱት አካባቢዎች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አካባቢዎቹ ጭር ብለው መዋላቸውንም የዓይን እማኞች ገለጻ ያስረዳል፡፡

በካራቆሬ ኬንቴሪ በተባለው የከተማዋ ክፍል ደግሞ የአደባባይ ተቃውሞ ጭምር መደረጉን ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዓለም ገና እና ሰበታ መካከል በሚገኘው ኬንቴሪ የተባለ ቦታ፣ ነዋሪው አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ሲያሰማ እንደነበር የዓይን እማኞች ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡ በሰልፉ ላይም ‹‹ወያኔ ሌባ!›› የሚል መፈክር ሲስተጋባ መዋሉም ተነግሯል፡፡ ነዋሪዎች ሰልፍ መውጣታቸውን ተከትሎ ፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው መድረሱን የገለጹት የዓይን እማኞቹ፤ ፖሊሶቹ ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውንም እማኞቹ ይናገራሉ፡፡

ህዝባዊ የስራ ማቆም አድማው በመሐል አዲስ አበባ የተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ ቢታይም፤ በኦሮሚያ ክልል በሰፊው የተተገበረው ይኸው አድማ በከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ጫና መፍጠሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ጫት፣ ፍራፍሬ እንዲሁም ሌሎች ምርቶችን የምትቀበለው አዲስ አበባ፤ በስራ ማቆም አድማው የተነሳ፣ ለጫትም ሆነ ለሌሎች ምርቶች እጥረት መጋለጧን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ እጥረቱ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን፤ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ምርቶችን በሚቀበሉ ሌሎች ከተሞችም መከሰቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.