አዋጁ ማንኛውንም የኃይል እርምጃዎች የመውሰድ መብት እንዳለው ተነገረ BBN

Standard

ትላንት ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ ማንኛውንም የኃይል እርምጃዎች የመውሰድ መብት እንዳለው ተገለጸ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይፋ አደረገው የተበላውን ይኸው አዋጅ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ አዋጁ በሚተገበርበት ወቅት የሚወሰዱ እርምጃዎችን ዘርዝረዋል፡፡ አዋጁ በስራ ላይ በሚቆይባቸው ቀጣይ ስድስት ወራት፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ በቡድንም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ትዕይን ማሳየት ወይም ተቃውሞን በምልክት መግለጽ፣ ጹሁፍ ማሳተም፣ መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስ እና ሌሎች ጉዳዮችን መከወን እንደሚያሳስር ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ክልከላዎች ተላልፎ የተገኘ ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደሚታሰርም መከላከያ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

አገዛዙ አዋጁን ተገን በማድረግ፣ ማንኛውም መገናኛ ዘዴ ማለትም ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን በፈለገው ሰዓት ሊዘጋ እንደሚችል የገለጸ ሲሆን፤ በሌላ በኩልም መንገድ ላይ የሚንቀሳቀስ ሰውም ሆነ ተሽከርካሪ በማንኛውም ሰዓት ፍተሻ ሊደረግበት እና በእጁ ላይ የተገኙ ንብረቶች ኤግዚቢት ሊደረጉ እንደሚችሉ አገዛዙ አሳውቋል፡፡ በአዋጁ ወቅት መደረግ የለባቸውም ተብለው የተዘረዘሩት ጉዳዮች በርካታ ሲሆኑ፤ በአጠቃላይ ግን አዋጁ ከመተንፈስ ውጭ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አግዷል ለማለት እንደሚቻል መግለጫውን የተከታተሉ ወገኖች ተናግረዋል፡፡

የዚህ አዋጅ መመሪያ፣ ከዚህ ቀደም ታውጆ ከነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአፈጻጸም መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተገልብጦ የመጣ ሲሆን፤ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ይህኛውም አዋጅ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በኃይል የማፈን ዓላማ እንዳለው ተነግሯል፡፡ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት የስርዓቱን ዙፋን መነቅነቁን የሚያምኑ ወገኖች፤ ‹‹የተነቃነቀውን ዙፋን መልሶ ለማቆም የሚደረግ ጥረት ነው›› ሲሉ አዋጁ የታወጀበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በስራ ላይ በቆየባቸው ወራቶች፣ በወቅቱ በሀገሪቱ ውስጥ ይካሄድ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ መግታት እንዳልቻለ ይታወሳል፡፡ የተቃውሞ ድምጾችን ለማፈን በድጋሚ የወጣው ይኸኛው አዋጅም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ደም የገበረለትን የስርዓት ለውጥ ጥያቄ ሊያዳፍነው እንደማይችል ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ‹‹ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል›› ሲሉ የተረቱት እነዚሁ ታዛቢዎች፤ ‹‹አገዛዙ ልፋ ቢለው ነው እንጂ፣ ህዝባዊ ማዕበል በአዋጅ አይገታም!›› በማለትም ወቅታዊውን ሁኔታ አመላክተዋል፡፡ ትላንት ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን፤ ከ15 ቀናት በኋላም የገዥው ፓርቲ ፓርላማ እንደሚያጸድቀው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ይመራል የተባለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን፤ በውስጡም ሌሎች አባላት አሉት ተብሏል፡፡ አባላቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ፣ የብሔራዊ ደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሰፋ አብዩ ናቸው፡፡ የአዋጁን መመሪያ ከሚያስፈጽሙት ባስልጣናት መካከል ሳሞራ የኑስ፣ ጌታቸው አሰፋ እና አሰፋ አብዩ የህወሓት ሰዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.