የታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌን ቃለ-ምልልስ ከእንባ ጋር ግብ-ግብ እየገጠምን አደመጥነው

Standard

በደህንነቱ ጌታቸው አሰፋ ልጆች የምድር ስቃይ እንዲቀበል ከተደረገባቸው ቦታዎች አንዱ ጊዮን ሆቴል በሚገኝ ምድር ቤት ውስጥ አንደነበርም ሐዘን እየናጠን ሰማን ።

.

አስገራሚ ነው ። ግዮን ሆቴል ፦ ከላይ በተነቆጠቆጡ ሳሎኖች አለማቸውን የሚቀጩና የሚደነክሩ ፤ ከስር በሚገኝ ጨለማ ክፍል ውስጥ ደግሞ አንዳርጋቸውን የመሰሉ ዘግናኝ ስቅየትን የሚቀበሉ ዜጎች የሚገረፉበት ስፍራ ። ያን የመሰለ በአትክልቶች የተዋበ ምድረ-ገነት ግዮን ሆቴል ፤ ያን የመሰለ በፍቅር የጦፉ ፍቅረኞችና የነገ ተስፋ ሕፃናቶች የማቦርቁበት መስክና የውሃ ገንዳ ያዘለ የመዝናኛ ስፍራ በስሩ ጉድ ይዟል ለካ ?

.

የጀርመኑ ሒትለር ሚስጥራዊ የፖሊስ ተቋም የነበረው (Gestapo)

አይሁዶችንና ” ጠላት ” የሚላቸውን ዜጎች አብዛኛውን ጊዜ አካላቸውን እየከተፈና እየበለተ የሚመረምረው ከመደበኛው የሀገሪቱ እስር ቤቶች ውጪ ባሉ ሆቴሎች ፣ ሆስፒታሎች ፣ የበጎ አድራጎት ሕንፃዎችና የማሕበረሰቡ መገልገያ የተለያዩ ተቋማቶች ውስጥ እንደነበር ያነበብናቸው ታሪኮች ነግረውናል ።

.

የሕወሓቱ ደህንነት ሐላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ….. የናዚውን Gestapo መሪ የነበረውን የሄነሪክ ሙለርን መርህና የስቅየት ዘዴን ከነስፍራው ጭምር የተጠቀመ ስለመሆኑ የምንሰማቸው ታሪኮች እያስረዱን ነው ።

.

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ገና እየተሳቀቅን ፣ እጃችንን በአፈችን ጭነን እየተገረምን የምንሰማቸው የስቅየትና የግፍ ትርክቶችን እንሰማለን ።

.

ማን ያውቃል … ከማሰቃያው ስፍራ ብዙነት ፣ ከአሰቃዮቹና ከአዛዦቹ ብዛት የተነሳ ልክ እንደጀርመኖቹ በአንዱ ጨለማ ክፍል ተረስተው ከነሰንሰለታቸው ደርቀው የቀሩ ዜጎች እንዳሉስ ?…..ማንም አያውቅም ። ጊዜ ግን እነዚህንም ያሳውቀናል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.