የአዲስ አበባው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ህዋስ የህወሀትን የማሰቃያ እና መሳርያ ማከማቻ ቦታ አወደመ

Standard

ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓ.ም አንድ የአርበኞች ግንቦት 7 የአዲስ አበባ ህዋስ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ከቀድሞ ናዝሬት አውቶቡስ ተራ አጠገብ የሚገኘውን የህወሓትን የድብቅ ማሰቃያ ቦታ እና የመሣሪያ ማከማቻ አወደመ። ቦታው ቀደም ባሉ ዓመታት የጉምሩክ መጋዘን ሆኖ ያገለግል ነበር። በቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ቦታው የሚያገለግለው በፌደራል ፓሊስ የመሣሪያ ግምጃ ቤትነትና በስውር ማሰቃያነት ነው።


በርካታ ወገኖቻችን ዓይኖቻቸው እየታሰሩ ወደዚህ ቦታ እየተወሰዱ ስቃይ (ቶርቸር) እንዲደርስባቸው በመደረጉ ለዘላቂ የአካልና የስነልቦና ጉዳት ተዳርገዋል። በዚህ ግቢ ውስጥ በደረሰባቸው ስቃይ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችም አሉ። በዚህ ግቢ ውስጥ በርካታ ወንድና ሴት እስረኞች እጅግ አሰቃቂና ኢሰብዓዊ በደል ተፈጽሞባቸዋል። በዚህ ግቢ ውስጥ በደሰረባቸው ስቃይ ምክንያት ዘር ማፍራት እንዳይችሉ የተደረጉ ወገኖቻችን በርካቶች ናቸው። በዚህ ፀረ ትውልድ እና ፀረ ኢትዮጵያ ተቋም ላይ ነው የአርበኞች ግንቦት 7 ህዋስ እርምጃ የወሰደው።


በተወሰደው ጥንቃቄ የተሞላበትና የተጠና እርምጃ ሳቢያ በግቢው ውስጥ የነበሩ መጋዘኞች ከነመሣርያዎቻቸው በእሳት እንዲጋዩ ተደርጓል፤ በተወሰደው እርምጃ ሳቢያ የተቀሰው እሳት በሁለት ሰዓታት ያህል ማጥፋት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ የተወሰደውን እርምጃ በዓይኖቹ እንዲያይና በህወሓት አምባገነን አገዛዝ የሚደርስበት ስቃይ ቁጭት እንዲወጣ እድል ፈጥሯል።

በተወሰደው እርምጃም አገር ወዳድ የፌደራል ፓሊስ አባላት የህቡዕ እርዳታ አድርገዋል።
ለወደፊቱም ተመሳሳይ እርጃዎች ሊወሰዱ እንደሚችሉ የአርበኞች ግንቦት 7 የአገር ውስጥ ህቡዕ አመራር ገልጿል። በተጨማሪም እያንዳንዱ አገሩንና ነፃነቱን የሚወድ ዜጋ በየተሰማረበት መስክ ሥርዓቱን የሚያዳክሙ የሕዝባዊ እምቢተኝነትና የሕዝባዊ አሻጥር እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ድል ከእኛ ነች እናሸንፋለን!!

በ ተክሉ ቀዲዳ

Advertisements

    ዝክረ ሰማእታት በ ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም ለተጨፈጨፉ ንጹሃን ዜጎች

Standard

   የዛሬ አስራ ሁለት አመት ልክ በዚህ ቀን ግንቦት  7, 1997 ዓ.ም የተደረገውን  ምርጫ መሸነፉን ተከትሎ አገዛዙ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በንጹሃን ዜጎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። አገዛዙ የፈጸመውን ምርጫውን የማጭበርበር ሂደት ለመቃወም አደባባይ ላይ በወጡ ዜጎች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የግድያ እርምጃ የወሰደበት ወቅት ነው። በዚህም ግድያ በርካታ ዜጎች ለሞትና ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል። በተለይ በአዲስ አበባ ላይ በአጋዚ ጦር በመታገዝ በርካታ ንጹሃን ዜጎች እንደወጡ ቀርተዋል። ህጻናት፡ ሴቶች፡ አዛውንቶችና ሮጠው ያልጠገቡ ወጣቶች ሳይቀሩ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። የዚህ ጭፍጨፋ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል።  የህወሃት መራሹ አገዛዝ ያደረሰብንን ይህን እና መሰል በደል መቼም አንረሳውም ፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

የወያኔ የአፈና መረብ አባላቶች ሥርዓቱን እየከዱ ነው 

Standard

        አብዛኛዉን አፋኝና ገዳይ አባላቶቹን ያጣዉና እያጣ የሚገኘዉ ብሐራዊ መረጃ በከፍተኛ ሚስጥር ከሐገር ዉጭ አሰልጥኖ ያስገባቸዉ አራት ስናይፐር አነጣጣሪ ገዳዮች፣ ሁለት ልዩ ኮማንዶ የጠለፋ ክፍል ስምሪቶች፣ ሁለት አይቲ ኢንጂነር መረቦች፣ ሁለት አለም አቀፍ ግራና ቀኝ ክንፍ ማንኛዉም አዉቶሞቢል አሽከርካሪዎች፣ ከድተዉ የደረሱበት እንደማይታወቅ በ2008 መጨረሻ ላይ ያሳወቀዉ የብሐራዊ መረጃ የሰዉ ሐይል እና ግንኙነት ክፍሉ በድጋሚ ባሳለፍነዉ ወር ሚያዚያ 2009 ላይ አንድ እስናይፐር አነጣጣሪና አንድ አይቲ ኢንጂነር ሰልጣኝ ባልታወቀ አካል መገደላቸዉን ለዉስጥ ክፍል ማሳወቁን ምንጮች ጠቆሙ። የ10 አለቃ ዝንዉ ክብረት እና የአይቲ ኢንጂነር የሳይበር ጥቃት ባለሞያዋ ወ/ሪት ሶስና ኤፍሬም የተባሉ ግለሰቦች ቻይናና ህንድ ተምረዉ የተመለሱ እንደነበሩ የጠቆመዉ ምንጫችን ይህን አይነት ድርጊት በመረጃዉ ቢሮ ዉስጥ የተለመደ ነገር እየሆነ ነዉ ሲል ጠቆሞዋል። በተያያዘ መረጃ በወታደራዊ ደህንነት የትግባር ክንፍ ተዋቅሮ የተላከ አንባ ( ANBA OPERATION ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለተግባር ተሰማርቶ የነበረ ቡድን በጎንደር ሊቦ ከምከም አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት በመመታቱ የተግባር መመሪያዉ ውድቅ  operation cancelled ) መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።በተጨማሪ ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት ሀላፊነት ያልወሰዱ እጅግ የታጠቁ ሐይሎች አስፋሪና ሰፋሪያኑን በቀዳሀሪፍ እካባቢ ገጥመዋቸውል በዚህ ድንገተኛና 23 ደቂቃ ብቻ በወስደ ውግያ ላይ ሸማቂያኑ ባደረሱት ጥቃት 3 የህወሀት ወታደሮች እና 2 የሱዳን ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን 8 ቱ ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል::

ልኡል አለሜ

በአገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የደህንት አባላት ድሬዳዋ ውስጥ ለ9 ቀናት የቆየ የማጣሪያና የመለያ ስብሰባ አካሂደዋል

Standard

ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የደህንት አባላት ድሬዳዋ ውስጥ ለ9 ቀናት የቆየ የማጣሪያና የመለያ ስብሰባ አካሂደዋል። በስብሰባው ላይ የህወሃት አባል ያልሆኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች፣ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የደህንነት አባላትን ለጠላት አጋልጠው በመስጠት ህይወታቸው እንዲያልፍ እያደረጉ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። የደህንነት አባላቱ ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ባልደረቦቻቸውን አጋልጠው እንዲሰጡ ማስጠንቀቂያ አዘል ማስፈራሪያ ተሰጥቷቸዋል። የደህንነት አባላት በተለያዩ ምድቦች ተከፋፍለው እርስ በርስ እንዲገማገሙ መደረጉን የገለጹት የኢሳት ምንጮች፣ በተለይም ድሬዳዋ እና ጅጅጋ ላይ ባልታወቀ ምክንያት የተገደሉትን ሁለት የጸረ ሽብር ግብረሃይል የደህንነት አባላትን መረጃ እንዲያወጡ ሲጨናነቁ ሰንብተዋል። ባለፈው አንድ አመት ከ6 ያላነሱ የደህንነት አባላት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ የደህንነት ባለስልጣናት ግድያውን የሚፈጽሙት የራሳችን የደህንነት አባላት ናቸው ብለው እንደተናገሩና በስብሰባው ላይ የተገኙት የደህንነት አባላቱ የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች እንዲጠቁሙ ተጠይቀዋል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት ግን ግድያው በመከላከያ የደህንነት አባላትና በመደበኛው የደህንነት አባላት መካከል ሳይፈጸም እንዳልቀረ ይገልጻሉ። በቅርቡ የተገደሉት ሁለቱ የጸረ ሽብር ግብርሃይል የደህንነት አባላት፣ በመከላከያ የደህንነት አባላት ተገድለዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። አንድ የደህንነት ባለስልጣን በስብሰባው ላይ “እንዲህ አይነቱ ግድያ የሚፈጸመው አስመራ ባሉ ተቃዋሚዎች ሳይሆን በእኛው አባላት ነው” ያሉ ሲሆን፣ እንዲህ አይነቱን ግድያ እና ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር እንዲፈጠር አንፈቅድም በማለት በሃይለቃል መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ተቋም፣ ከመከላከያ የደህንነት ተቋም ጋር የፈጠረው አለመግባባት እርስ በርስ እየተፈራሩ እንዲኖሩ እንዳደረጋቸው ምንጮች ገልጸዋል። የዋናው የደህንነት መስሪያ ቤቱ ስብሰባ ከጠራህ በሁዋላ፣ ስብሰባውን ሳትጨርስ በተለያዩ መንገዶች የምትገደልበት ሁኔታ እየተፈጠረ በመሆኑ፣ በጋራ ሆኖ ስብሰባ ማካሄድ እየቸገረ ነው የሚሉት እነዚህ ምንጮች፣ አብዛኞቹ የሚገደሉት ከዋናው ደህንነት ሰራተኞች በመሆኑ፣ ገዳዮቹ የመከላከያ የደህንነት አባላት ናቸው ብለው እንዲያምኑ እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ። “በደህንነት አባላቱ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ሙከራ ከማድረግ ይልቅ ችግሩን ከብሄር ጋር አያይዞ ለማቅረብ መሞከር ራስን ማታለል ነው፣ ችግሩ የራሳቸው የውስጥ ችግር በመሆኑ መፍትሄውንም መፈለግ ያለባቸው ራሳቸው ናቸው” ሲሉ ያክላሉ።

​ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መራባቸው በተነገረ በሳምንት 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮች ኢትዮጵያ መግባታቸውን አነጋገረ

Standard

ሚያዚያ 24 ቀን 2009 ዓም ጠዋት በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሾፌሮች ገልጸዋል። በጅቡቲ ወደብ 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮች የተራገፉ መሆኑን የሚገልጹት የአይን እማኞች፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑትን ታንኮች የጫኑ ሎቤድ መኪኖች ወደ ደብረዘይት ተንቀሳቅሰዋል። ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መራባቸው በተነገረ በሳምንት በእርዳታ እህል ፋንታ ይህን ያክል ቁጥር ታንክ ወደ አገር ውስጥ መግባቱ ግርምት እንደፈጠረባቸው ሾፌሮች ገልጸዋል። ገዢው ፓርቲ በአገር ውስጥ ከገባበት የፖለቲካ አጣብቂኝ ለመውጣት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊያደርግ እንደሚችል የተለያዩ ፍንጮች እየታዩ ነው። ምላሻቸው እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ የስራዊት ምልመላ ለማድረግ ተደጋጋሚ ማስታወቂያዎች መውጣታቸው እንዲሁም በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊሲ እንከተላለን በመላት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ትግራይ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው፣ አገዛዙ የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቀየስ ሊጠቀምበት እንደሚችል ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ።

በ በሀይሉ ዳምጤ

ልዩ የተማሪወች ንቅናቄ ተጀመረ 

Standard

       በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪወች የነፃነት ትግል ፅሁፎች በት/ቤት ሰሌዳወች ላይ እየፃፉ ነው፤ የሌሎች ዩኒቨርስቲወች ተማሪወች ሁለገብ የትግል ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል።በት/ቤት ሰሌዳወች ላይ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ አንድ ኢትዩጲያ የሚሉ ፁሁፎች እየተፃፋ ሲሆን በእነዚህ ፁሁፎች ብቻ አስተማሪወችና የህወሓት ቅጥረኛ ጆሮጠቢወች፣ የት/ቤቱ የህወሓት/ወያኔ አስተዳደር ክፋኛ መረበሻቸው ታውቋል።” የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ህልም እውን ይሆናል!” “የመሪያችንን ትዕዛዝ ለማስፈፀም ለነፃነት እስከሞት!!” በማለት የነፃነት ትግሉን እያቀጣጠሉ ያሉት ተማሪወች በመላ ኢትዩጲያ ዩኒቨርስቲወች ነፃነት ፈላጊ ተማሪወች የሚቀጣጠል ትግል እንደጀመሩ ይናገራሉ።የወያኔ ሰላዩች እንደሚከታተሉን እኛም በትክክል እየተከታተልናቸው እንገኛለን የህቡዕ ቡድኑን መዋቅር በማስፋት ትግላችን መልኩን እየቀየረ በእብሪት ጥጋብ ልቡን ያሳበጠውን የወያኔ ወንበዴ ቡድን መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣትና እንዳይረጋጋ አድርጎ በመረበሽ ለነፃነት እስከህይወት መስዋዕትነት የደረሰ ትግል በአንድነት አድርገን ነፃነታችንን እንቀዳጃለን በማለት ሁሉም በተግባር ለነፃነት እንዲነሳ ጥሪ ያስተላልፈዋል።

በ ከታ ማኛ

በደሴ ግዳጅ ከሕዝብ ጋር አንጣላም ያሉ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች መሣሪያ ሊገፈፉ ነው

Standard

ዓባይን በእግር የሚሻገሩ ሰዎችን ለመከልከል የተለቀቀው ግድብ ጉዳት አደረሰ፤ሚዚያ 2 ቀን 2009 ዓ.ም፤ በደሴና አካባቢው ያሉ የታጠቁ ሚሊሻዎች ራቅ ወደ አሉ አካባቢዎች ለተልዕኮ አንሔድም በማለታቸው ትጥቃቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዋል፡፡ ዛሬ ጠዋት አካባቢ ከደሴ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ሚሊሻዎች ያስታጠቀን ሕዝብ በመሆኑ መሣሪያ አንመልስም በማለታቸው ከአስተዳደር አካላት ጋር ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡ በደሴ ከተማ የሲቪል ፖሊሶች ታማኝ አይደላችሁም በሚል ግምገማ መሣሪያ እንዳይዙ ታግደዋል፡፡ ከሰሞኑ መሣሪያ የተከለከሉት ፖሊሶች እገዳው እስከመቼ ድረስ ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም፡፡

በተያያዘ የደሴ ከተማ ነጋዴዎች ሥራ ባለመሥራታችን ግብር ልንከፍል አይገባም የሚል ተቃውሞ አንስተዋል፤ መምህራን በበኩላቸው አመጻቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ ሰምተናል፡፡

በሌላ በኩል በዓባይ ድልድይ ምክንያት ከሁለት ተከፍላ የሰነበተች የባሕር ዳር ከተማ ለዜጎቿ ስቃይ ሆናለች ተብሏል፡፡ ድልድዩ በመዘጋቱ ምክንያት የዓባይን ወንዝ በዋና እንዲሁም ድንጋይ ባለበት አካባቢ ደግሞ በእግር ለመሻገር መፍትሔ ያደረጉት የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የጨርጨራ ግድብ ተከፍቶ ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡ በዋና እና በእግር የሚሻሩ ሰዎችን ለመከልከል የተለቀቀው ግድብ ምክንያት በቀበሌ 10 እና 11 የዓባይ ወንዝ አጠገብ የጓሮ አትክልቶች ተጠራርገው ተወስደዋል ብለውናል እማኞቻችን፡፡ ከወንዙ ዳር አንድ ኪሜ ርቀት ላይ ያለ የአትክልት ቦታ ድረስ ጉዳት አድርሷል ያሉት ምንጮች በድንገት የተለቀቀው ግድብ ከባሕር ዳር ራቅ ብለው ባሉ ገበሬዎች ማሣ ላይና የሰው ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

©Et