ግልፅ ደብዳቤ ከቄሮ “ክፍት ደብዳቤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሙሉ” ከኦሮሞ ቄሮ የተላለፈ ጥሪ

Standard

ከሁሉም አስቀድመን ባላችሁበት ሰላምታ ይድረሳችሁ።

ሁላችንም እንደሚናውቀው የኦሮሞ ቄሮዎች ህይውታችንን መስዋዕት አዲርገን የኦሮሞ ህዝብ መብትና ብሄርቤረሰቦች እኩልነት የተረገጋጠባትን ኢትዮጽያ ለመመስረት ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነው። የኦሮሞ ህዝብ ሰላማዊ ትግል ይህችን አገር እየቀየራት ይገኛል።

ይሁን እንጅ አንባገነን የሆኑ የTPLF ጥቂት ኮንትሮባንዲስቶች ቡድን አገሪቷን ለማዝረፍ በተሃድሶ መሪዎች ና በቄሮ የተዘጋባቸዉን የዝርፍያ መንገድ መልሰዉ ለመቆጣጠር ፣ አገርቷን በጦር ሀይል ለማቆጠጣር አስቻኳይ ግዜ አወጅ እያዋጁ ይገኛሉ። ይሄ አዋጅ በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት አይኖረዉም።

የተከበራችሁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ኮንትሮባንድስቶች አገሪቷን ለመበዝበዝ እና ለመበታተን በኦሮሞ ህዝብና በመላው ብሄርቤረሰቦች ላይ የታዋጀ አዋጅ እንዲሰረዝ የበኩላችሁን የዜግነት ግደታ በመወጣት አገሪቷን ከዉድቀት እና ከመበታተን እንድታድኑ የኦሮሞ ቄሮ በዚህ ደብዳቤ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ከዚህ እልፎ አዋጁ የሚጸድቅ ከሆነ የኦሮሞ ቄሮና ህዝብ የአፀፋ ምላሽ ተጠያቂዎቹ TPLF ና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መሆናችሁን እናሳስባለን።

ከሰላምታ ጋር

የኦሮሞ ቄሮ”

Advertisements

ህወሃት ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይሰራ ማድረግ ቀዳሚ ተግባራችን ነው።

Standard

ከአርበኞች ግንቦት 7

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መላው ህዝባችን እየጠየቀ ያለውን የእኩልነትና የነጻነት ጥያቄ በወታደራዊ ሃይል ለመጨፍለቅና ላለፉት 27 አመታት የኖርንበት አይነት የግፍና የመከራ ዘመን ለማስቀጠል ወስኖ እንቅስቃሴ ለማድረግ መዘጋጀቱን የካቲት 8 ቀን 2010 ይፋ ባደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አረጋግጦአል።

በመላው አገራችን የተቀሰቀሰውን ይህንን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመጨፍለቅ ያስችለኛል ብሎ ህወሃት ያወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበትን ወቅት ብንመለከት፤ የኢህአደግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ አገሪቱ ለገባቺበት የፖለቲካ ቀውስ ሙሉ ሃላፊነት ወስዶ መፍትሄ ፍለጋ ከሁሉም ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር እንደሚነጋገርና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ “ውሳኔ አስተላልፌያለሁ” ባለ ጥቂት ወራት ውስጥ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ላለፉት 6 አመታት የአገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትርነትና የኢህአደግ ሊቀመንበርነትን ሥልጣን ይዞ የቆየው ሃይለማሪያም ደሣለኝ ለዚህ ውሳኔ ተገዥ በመሆን “ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር” ለማድረግ ይቻል ዘንድ “ሥልጣኔን በገዛ ፈቃዴ ለቅቄያለሁ” ብሎ ባስታወቀ ዕለት ማግሥት መሆኑ በሰፊው እያነጋገረ ነው ።

ህወሃት/ኢህአደግ በህይወት ዘመኑ ሁሉ ለቃሉ እንደማይታመን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ የሚያውቅ ቢሆንም የሃይለማሪያም ደሣለኝ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄውን ይፋ ከማድረጉ ጥቂት ቀናት በፊት ጀምሮ አንድም ቀን እስከነመኖራቸው አገዛዙ ምንም አይነት እውቅና ሰጥቶ የማያውቅ በርካታ የፖለቲካና የሂሊና እስረኞችን መፍታት በመጀመሩ፡ ህወሃቶችና የሚመሩት መንግሥት ወደ ሂሊናቸው ተመልሰው ህዝባችን ለአመታት ሲታገልለትና ውድ ህይወቱን ሲገብርለት የኖረውን የዲሞክራሲ ጥያቄ ዕልባት እንዲያገኝ የራሳቸውን አስተዋጾ ለማድረግ የተዘጋጁ መስሎት አብዛኛው ህዝብ በትልቅ ተስፋና ጉጉት ሁኔታውን ሲከታተል ሰንብቶአል።

እስከ አገባደድነው ሳምንት አጋማሽ በአብዛኛው የኦሮሚያ፤ የአማራና አንዳንድ የደቡብ ከተሞች ህዝብ አደባባይ በመውጣትና ቤት ውስጥ በመቀመጥ አድማ ሲጠይቅ የነበረውም ይህ የተጀመረው እስረኞችን የመፍታት በጎ ጅምር ተፋጥኖ እስር ቤት የቀሩት ፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲለቀቁና ሁሉንም ያቀፈ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀመርና አገራችን ከገባቺበት የፖለቲካ አጣቢቅኝ እንድትወጣ መፍትሄ እንዲፈለግ የሚያሳስብ ነበር።

ከፍጥረቱ ጀምሮ ለኢትዮጵያ አገራችንና ለህዝቧ ደንታ ኖሮት የማያውቀው ወያኔ ግን ህዝብ ተስፋ ያደረገውን ይህንን እድል ለማጨለምና የታገለለትን ዓላማ ለመቀልበስ ያስችለኛል ብሎ ያመነበትንና ከአመት በፊት ሞክሮ ያልተሳካለትን ወታደራዊ አገዛዝ አገራችን ላይ መልሶ ለማስፈን ህዝባችንን እያስቆጣ ያለ ይህንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደገና አውጆአል።

የንቅናቄያችን ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልከተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ህወሃት ላለፉት 27 አመታት በአገራችንና በህዝቧ ላይ ያመጣውን መዓትና የወረደውን ግፍ ለሀገር ሠላም ሲባል በብሄራዊ እርቅ ስሜትና እነርሱንም ባሳተፈ የድርድር ሄደት እንዲፈታ በሠላማዊ ህዝባዊ ትግል እየጠየቀ ባለበት ወቅት፣ ይህ አዋጅ መታወጁ ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል የሚሄድበት ርቀት ምን ያህል የእብደት መንገድ እንደሆነ የሚያሳይ” ብቻ ሳይሆን፣ በህወሃት ውስጥ ያሉ የአገዛዙ ቁንጮዎች እንወክለዋለን ሲሉ የኖሩትን የትግራይ ህዝብ ጨምሮ ከተጠናወታቸው የግል ጥቅም አስበልጠው የሚጨነቁለት ህዝብ ወይም አገር ፍቅር ስሜት የሚባል ነገር የሌላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

ይህንን ሃቅ ያልተረዱ አንዳንድ ወገኖች እንደሚከራከሩት ህወሃት ውስጥ ትንሽም ቢሆን የህዝብና የአገር ፍቅር ስሜት ያላቸው የአመራር አባላት ቢኖሩ ኖሮ፣ ከሁለት አሥርተ አመታት በላይ ለዘለቀ ጊዜ ልዩ ልዩ የጠላትነት ታፔላ እየተለጠፈለት በጭካኔ ሲጨፈጨፍ ፤ ሲታሠር ፤ ሲገረፍ ፤ ከትውልድ መንደሩና ቄዬው ሲፈናቀልና ሲሰደድ የኖረው ህዝብ ለሠላም ሲል የተፈጸመበትን መከራና ስቃይ ፋይሎችን ሁሉ በብሄራዊ እርቅ ዘግተን እናንተንም ጭምር ያካተተ የሽግግር ምዕራፍ ይከፈት ብሎ ሲጠይቅ “ምን ታመጣለህ?” በሚል እብሪትና ጀብደኝነት ከራሱ ከህዝብ አብራክ የወጣውን የመከላኪያ ሠራዊት ህዝብ ላይ ለማዝመትና አገራችንን ወደ የርስ በርስ ብጥብጥ ለመክተት እንዲህ አይነት አፋኝ አዋጅ ባላወጀ ነበር።

ታጋሽ፣ ጨዋና አስተዋይ ይሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ሲፈጸምበት የኖረውን መከራና ስቃይ ሁሉ ለሠላም ሲል ይቅር ብሎ ለህወሃት የይቅርታ እጁን የዘረጋው፣ ድርጅቱ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ በመብቱ፣ በብሄራዊ ጥቅሙና በሉአላዊነቱ ላይ ሲፈጽማቸው የኖረውን ግፍና ወንጀሎች ሁሉ ሳያሳምሙት ቀርተው አልነበረም። ወይንም ደግሞ ህወሃቶች እንደሚያስቡት የሚተማመኑበት ወታደር ብዛትና መሣሪያ ጋጋታ የጀግንነት ወኔውን ሰልቦት በባርነት እየተረገጠ መገዛትን ፈቅዶ አይደለም። የአጋዚ ጦር በጠራራ ጸሃይ የሚፈጽምበትን ጭፍጨፋ እየተመለከተ ግንባሩን ሳያጥፍ ላለፉት ሶስት አመታት ባዶ እጁን “ነጻነቴን መልስልኝ!” እያለ ከአገዛዙ ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠ ያለው ለዚህ ምስክር ነው።

አርበኞች ግንቦት 7 ደጋግሞ ለመግለጽ እንደሞከረው ህወሃት እየገጠመው ከመጣው አገር አቀፍ ህዝባዊ ተቃውሞ በተጨማሪ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረው የጥቅምና የሥልጣን ሽኩቻ አንድነቱ የተናጋ ድርጅት ከመሆን አልፎ በገዛ አገራቸውና ወገናቸው ኪሳራ እስከ ዛሬ መሣሪያ ሆኖ ሲያገልግሉት የኖሩት የኢህአደግ አባል ድርጅቶች (በተለይም ኦህዴድና ብአዴን) ከአሁን ቦኋላ “የበላይነትህን አንቀበልም” ብለው አጣብቅኝ ውስጥ የከተቱት ድርጅት በመሆኑ፣ እንኳን ይህንን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመላው አገሪቱ ላይ ሊያስፈጽም ቀርቶ እንደ ድርጅትም ጸንቶ ለመቆየት የሚያስችለው አቅም እንደለለው ያምናል።

ይህንን አቅሙን የተረዱት ምዕራባዊያን ወዳጆቹ ሰሞኑን ባወጡት ጠንከር ያለ መግለጫ በአጉል ትዕቢትና ጀብደኝነት ተጠምዶ እራሱንና አገሩን ወደ ከፋ አደጋ ከመውሰድ እንዲታቀብና አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአስቸኳይ አንስቶ ከሁሉም ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመደራደር አገራዊ መፍትሄ እንዲፈልግ አሳስበውታል። የህወሃት መሪዎች ምዕራባዊያን ወደጆቻቸውና የኢትዮጵያ ህዝብ እያቀረቡላቸው ያለውን ጥሪ ተቀብለው የህዝባችንን የለውጥ እንቅስቃሴ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል እርምጃ ቢወስዱ እራሳቸውንና ድርጅታቸውን ከህግና ከታሪክ ተጠያቂነት ያድናሉ ፤ የለውጡ አካልም በመሆን ህልውናቸውንና ጥቅማቸውን ለማስከበር እድል ያገኛሉ። ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው ለህዝብ እንጨነቃለን የሚሉ አባላትና ደጋፊዎቻቸው በሙሉ አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ ተጽዕኖ ሊያደርጉ ይገባል።

አርበኞች ግንቦት 7 ህወሃት ህዝባችንን ለማፈንና የባርነት አገዛዙን መልሶ ለማስፈን ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደ ከዚህ በፊቱ ፍጹም ሊሠራ የማይችል መሆኑን ለማሣየት ለመብቱና ለነጻነቱ እየተፋለመ ካለው ህዝባችን ጎን ቆሞ በሁሉም የትግል መስክ ተግቶ ይሠራል። በዚህም የተነሳ የኢህአደግ አባል ድርጅቶች ውስጥ እየታዩ ያሉ አንዳንድ የለውጥ ሃይሎች የሚያደርጉትን ጥረት ተስፋ አድርገው የሚጠባበቁ ካሉ፣ ይህ አዋጅ እነርሱንም ጭምር ጭዳ ለማድረግና በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ወታደራዊ አገዛዝ ለማስፈን የታለመ መሆኑን ተገንዝበው አዋጁ እንዳይሰራ ለማድረግ ከህዝባችን ጎን እንዲሠልፉ ወገናዊ ጥሪውን በየደረጃው ላሉ ለነዚህ የኢህ አደግ አባላትና ደጋፊዎች ያቀርባል ። ኦህዴድንና ብአዴንን በመወከል የአገሪቱ ፓርላማ አባላት ሆነው በማገልገል ላይ ያሉ የህዝብ ተወካዮች ነን የሚሉ ወገኖችም የህዝብን መብትና ስብዕና የሚጋፋ ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማው እንዳይጸድቅ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ያሳስባል። ይህንን ታሪካዊ ሃላፊ ነታቸውን መወጣት ተስኖአቸው አዋጁ እንዲጸድቅ ካደረጉ፣ በአዋጁ ምክንያት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ለሚደርሰው በደል ከህወሃት እኩል ተጠያቂ እንደሚሆኑ እንዲገነዘቡም ያስጠነቅቃል።

ከህዝብ አብራክ የወጣው የአገራችን መከላኪያ ሠራዊት ፤ የፖሊስና የደህንነት ተቋም አባላትም በሙሉ ህወሃት የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ሲል ህዝባችንን እርስ በርስ ለማጋጨትና አገራችንን ወደ ትርምስ ለመውሰድ ያወጣውን ይህንን አፋኝ አዋጅ ፈጽሞ ሥራ ላይ እንዳይውል እንዲከላከሉና የሚሠጣቸውን ተእዛዝ እንዳይቀበሉ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ወገናዊ ጥሪውን ያቀርብላቸዋል።

የትግራይ ህዝብን ጨምሮ መላው የአገራችን ህዝብ መውደቂያው የተቃረበው የህወሃት አገዛዝ ከፊት ለፊታችን የደቀነውን አደጋ በጋራ ለመመከትና ሁላችንም እኩል ተጠቃሚ የምንሆንባት አገር ባለቤት ለመሆን የሚደረገውን ትግል እስከመጨረሻው የድል ቀን ድረስ በቁርጠኝነት እንዲገፉ ንቅናቄያችን ወገናዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 16/2010) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ የበጀት እጥረት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ

Standard

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 16/2010) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ የበጀት እጥረት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ። ከፍተኛ ገቢ የሚጠበቅበት የመሬት ሊዝ ጨረታ ላለፉት 8 ወራት አልተካሄደም። መስተዳድሩ በግማሽ አመቱ እሰበሰባለሁ ብሎ ካቀደው ማግኘት የቻለው ከግማሽ በታች ነው።እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ የተሰበሰበው ገቢ የአስተዳደሩን የመደበኛ ወጪ ከመሸፈን የሚያልፍ አይደለም።በአመቱ ይሰራሉ ተብለው በእቅድ የተያዙ ካፒታል ፕሮጀክቶች ከእቅድ እንደማይዘሉ ጨምረው ገልጸዋል። በሃገሪቱ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ፣የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣የንግድና አገልግሎት ተቋማት መዳከም፣ነጋዴውና የከተማው ነዋሪ ለመስተዳድሩ ግብር ለመክፈል ፍላጎት ማጣትና የአስተዳደሩ ሰራተኞች በፍላጎት ለመስራት ዝግጁነት ማጣት ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተመልክቷል። በሀገሪቱ ተፈጠረው የጸጥታ ችግርና የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የውጭ ኢንቨስተሮች ተሳትፎም እንደቀነሰ ማወቅ ተችሏል። በ2009 በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በተሰናዳው የአለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ከ20 ሀገሮች በላይ የሚገኙ 160 በላይ የውጭ ኩባንያዎች የተሳተፉ ቢሆንም ፣ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው አውደ ርዕይ የተሳታፊዎች ቁጥር እንደሚቀንስ ታውቋል ። ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳዩት 11 ሃገራት ብቻ እንደሆኑም መረዳት ተችሏል።በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከፍተኛ ገቢ የሚሰበስብበት የመሬት ሊዝ ጨረታ ላለፉት 8 ወራት ማካሄድ እዳልቻለ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስመልክቶ፣ የተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል

Standard

እንግሊዝ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠሪ ሚኒስቴሯ በኩል እንዳስታወቀችው፣ የጠ/ሚኒስቴሩን ስልጣን መልቀቅ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የተቃወመች ሲሆን፣ አዋጁ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችንና ህገ መንግስቱን የሚጥስ ነው ስትል ተቃውማለች።

ከዚህ ይልቅ ሊሆን የሚገባው. . . የጠ/ሚኒስቴር ቦታውን እየተከሰተ ያለውን ለውጥ ሊያስቀጥል የሚችል ሰው በህጉ መሰረት ባስቸኩዋይ ማስቀመጥና፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር ነው።

ይህም ወደ ሰላማዊ ሽግግር የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ ነው፣ ስትል አሳስባለች።

ሙሉ መግለጫውን ከታች ያንብቡ

#UK_Embassy_Addis_Ababa #Asham_Media #አሻም_ሚዲያ

UK concerned over State of Emergency in Ethiopia

~~~~~~~//~~~~~~~//~~~~~~//~~~~~

Minister for Africa Harriett Baldwin gave a statement on the Ethiopian State of Emergency.

Minister for Africa Harriett Baldwin said:

“The UK has been following closely the past week’s events in Ethiopia. We share outgoing Prime Minister Hailemariam’s view that this is a concerning time for a country that is our friend and our partner. We welcome the commitment to an orderly process of political change in line with the constitution, as well as his repeated support for a continued reform process.

Against that backdrop we are, however, concerned and disappointed by the decision to impose a new State of Emergency. It sends a discouraging signal to the international community and foreign investors. We strongly hope that the announcement does not signal a reversal in Ethiopia’s recent moves towards reform, and that it will be in place for as short a time as possible. In implementing the State of Emergency, we urge the Government of Ethiopia to ensure that human rights and the constitution are respected. Widespread use of detention powers and internet blockages should be avoided.

We call on the Government to ensure a rapid, peaceful, transparent and constitutional transition to a new leadership that continues and accelerates the reform process. The UK is a long-term friend of Ethiopia and we continue to stand ready to support a purposeful and progressive reform agenda.

የአዉሮፖ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ

Standard

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 12/2010) የኢትዮጵያ መንግስት ከሁሉም ወገኖች ጋር ሁሉን አቀፍ ንግግር እንዲጀምር የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ። የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በድንገት ከስልጣን የመልቀቅ ርምጃም በሃገሪቱ ያልተጠበቁ ሁኔታዎችን መደቀኑን ህብረቱ አስታወቋል። የአውሮፓ ህብረት ዛሬ ባሰራጨው በዚህ መግለጫ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንደገና መታወጁም በዘላቂ መፍትሄ ጥረቱ ላይ አደጋ መደቀኑንም ገልጿል። በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚዋቀረው መንግስት የተጀመሩ በጎ ርምጃዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሙሉ አቅም ሊኖረው እንደሚገባም አሳስቧል። ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር የሚደረግ ንግግር ለቀውሱ ዘላቂና ሰላማዊ መፍትሄ እንደሚያመጣ የገለጸው የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት፣ተቃዋሚዎች፣መገናኛ ብዙሃንና ሲቪል ሶሳይቲ መካከል ንግግር እንዲጀመርም ጥሪ አቅርቧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደገና ተመልሶ መምጣቱ ዘላቂ መፍትሄ ፍለጋውን ለአደጋ ማጋለጡን ሆኖም በአጭር ጊዜ ገደብ ውስጥ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ ቀርቧል። በሃገሪቱ ሕገ መንግስት የሰፈሩ ሰብአዊ መብቶች እንዲሁም መሰረታዊ ነጻነቶች እንደተጠበቁና የአመጽ ድርጊቶችም እንዲወግዱ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይና ሴኪዩሪቲ ፖሊሲ ቃል አቀባይዋ ካትሪን ሬይ በኩል ባወጣው መገለጫ አሳስቧል።

የጠቅላይ ተጠቅላይ ጨዋታ (ኤርሚያስ ለገሰ)

Standard

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀጥሎ የኢትዬጲያን የፓለቲካ አየር የሞላው የሚቀጥለው “ጠቅላይ/ ተጠቅላይ” ማን ይሆናል የሚለው ነው። ይህንን ጉዳይ ሰዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ይመለከቱታል። በተለይም በማህበራዊ ድረገጾች ካሉት ፍትጊያዎች አንዱ በዚህ ዙሪያ ያለው እሰጣ ገባ ሆኗል። በአንድ በኩል ስርነቀል የስርአት ለውጥ ለማምጣት እየታገልን ባለንበት ሰአት በዚህ አነስተኛ አጀንዳ ዙሪያ ለምን ጊዜያችንን እናጠፋለን የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በሌላ በኩል ከራሳቸው እምነት፣ ጥቅም እና ፍላጐት በመነሳት ” እከሌ ጠቅላይ መሆን አለበት!” የሚለውን የሚገፋም አልታጡም።

የትግራይ ነፃ አውጪ የፌስቡክ ካድሬዎች በሁኔታዎች ተደናግጠው ቢጠፉም ከእናት ፓርቲያቸው ጋር እያሴሩ መሆኑ የሚደበቅ አልሆነም። ትኩረት ለሰጣቸው በሕዝብ ፊት የሚደሰኩሩትና ከመጋረጃ ጀርባ የሚሰሩት የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ለየቅል መሆኑን ማየት ይቻላል።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እና አንድ ወዳጄ ሰሞኑን ተወዳጅ ሆና ከአብዛኛው አንደበት በተነገረችው አዝናኝ ቃል ተጠቅሞ ” ኮካዎች ሸሹ ወይስ አፈገፈጉ?” ብሎ ጠይቆኝ ነበር። እኔም ” ኮተታም ካድሬዎችን በዝንብ ከፍ ካለም በጆፌ አሞራ ልትመስላቸው ትችላለህ። ደም እንደ ጐርፍ ሲወርድና የሰው ህይወት በአጋዚ ሲቀጠፍ ጐርፍ ሆነው ይመጣሉ” አልኩት። እውነት ለመናገር ኮካዎች በደም ካልሰከሩ እስትንፋስ ያላቸው አይመስለኝም።

ያም ሆነ ይህ የትግራይ ነፃ አውጪ ” የጠቅላይ/ተጠቅላይ” ጨዋታን የሚመለከተው ከራሱ ህልውና አንፃር ብቻ ነው። የዘረጉት ሕግና የአፈና ስርአት የፓለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነታቸውን እስካረጋገጠላቸው ድረስ ለተፈፃሚነቱ በትጋት ይንቀሳቀሳሉ። ሕገ መንግስቱን ለማስከበር በሚል ሽፋን የፓርቲያቸውን የበላይነት ለማረጋገጥ የቻሉትን በሙሉ ያደርጋሉ። የተፈጠረባቸውን ቀውስ ለመደበቅ በሚያደርጉት መፍጨርጨር መዳመጥ ያለባቸውን ለመዳመጥ ህገ መንግስት በመጠበቅ ስም አስፈሪ ተኩላ ይሆናሉ። ለዚህ እንዲያግዛቸው የራሳቸው የጫካ ፕሮግራም ግልባጭ የሆነውን ሕገ መንግስት እንደ ጋሻ ይጠቀማሉ። በተጨማሪም በዣንጥላነት እያገለገላቸው ያለውን የኢህአዴግ ህገ-ደንብ ያለምንም ለውጥ እንዲተገበር ያደርጋሉ።

በመሆኑም የጠቅላይ /ተጠቅላይ ጨዋታን በዋናነት ማየት የሚገባን የትግራይ ነፃ አውጪ ፍላጐት ምንድነው ከሚለው አንፃር ይሆናል። ህውሓት ፓለቲካዊ ሞቱን ለመሞት እያጣጣረ ቢሆንም የፀጥታና የስለላ መዋቅሩ ገና አልተነካም። አሁንም ማሰር፣ መግደል፣ መሰወር ይችላል። አሁንም ህገ መንግስቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚል ሰበብ እየሞተ ያለውን የፓለቲካ መዋቅር አዛዥና አናዛዡ የፀጥታና ስለላ መዋቅሩ ነው። እያንዳንዱ የፓርላማ አባላት ጋር እየደወለና በአካል እየሔደ ” አስቸኳይ ግዜ አዋጁን ባታፀድቅ በሞቀው ህይወትህ ፍረድ። እንደውም ተቃውሞ እያስተባበርክ ያለኸው አንተ መሆንህን ደርሰንበታል” እያለ ያስፈራራል። ለምሳሌ የስለላው መዋቅር አባል የሆነው አስመላሽ ወልደስላሴ ከስብሰባው በፊት በቀጭኑ ሽቦ ” አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፓሊሲ ጉዳይ ነው” ማለት በቂው ሊሆን ይችላል። በኢህአዴግ መንግስታዊ መመሪያም ሆነ የድርጅት ህገ ደንብ አንፃር ” የፓሊሲ ጉዳይ ነው!” ከተባለ በተፃራሪው መቆም ፈፅሞ አይቻልም። እናም የፀጥታና ስለላ መዋቅሩ የፓለቲካ አመራሩን እንደ ህዝብ ግንኙነት ተጠቅሞ የፈለገውን በሀይል ሊፈፅም ይችላል።

ወደ ጠቅላይ ተጠቅላይ ጨዋታ ስንመለስ ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው የትግራይ ነፃ አውጪ ሁለት ሰነዶችን መዞ ያወጣል። እነዚህም የኢህአዴግ ሕገ መንግስትንና ህገ ደንቡ ናቸው። እስቲ እያንዳንዱን በተናጠል እና በተዛምዶ እንመልከት።

የኢህአዴግ ሕገ መንግስት

አስቀድሞ እንደተገለጠው የትግራይ ነፃ አውጪ ሁሉንም መቆጣጠር የሚፈልገው ” ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን” ለማስጠበቅ በሚል እንደሆነ ይታወቃል። በተለይም የህገ መንግስቱ አንቀፅ ዘጠኝ እየተጠቀሰ የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሀላፊነት አለብን የሚባለው በዚህ ምክንያት ነው። አንቀፅ ዘጠኝ የኢህአዴግ ህገ መንግስት የአገሪቱ የበላይ ህግ መሆኑ፣ ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ይደነግጋል። በሕገ መንግስቱ ከተደነገገው ውጭ በማንኛውም አኳኃን የመንግስት ስልጣን መያዝ እንደተከለከለ ይገልጣል።

ምንም እንኳን የትግራይ ነፃ አውጪ ቅጥፈት ሞራላዊ እሴት ብቻ ሳይሆን የአገዛዙ ዋልታና ማገር መሆኑ ቢታወቅም እስከጠቀማቸው ደረስ ” ሕገ መንግስቱ ይከበር” ማለታቸው አይቀርም። ስለዚህም በደብረፂዬን መሪነት በፀጥታና ስለላ የበላይነት የያዘው ፓርቲ ” የጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰያየም!” የሚለውን የሕገ መንግስት አንቀፅ 73 ላይ ሙጭጭ ማለቱ አይቀርም። በአዋቂነት ውስጥ ሆነው በኩራት ይገልጡታል። በነገራችን ላይ አንቀፅ 73 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዬች ምክርቤት አባላት መካከል ይመረጣል ይላል።

በእኔ እምነት የደብረፂዬን ፓርቲ ይሄን የህገ መንግስት አንቀፅ የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ነው ማለቱ አይቀርም። በተደጋጋሚም ” ህገ መንግስቱ ይከበር!” የሚል ከበሮ መደለቅ ይጀምራል። እናም ይሄ ከሆነ ዘንዳ ከውሳኔው የማያሻማ ቁምነገሮችን ማውጣት ይቻላል።

የመጀመሪያው ቁምነገር ” ጠቅላይ/ ተጠቅላይ” የሚሆነው ግለሰብ የግዴታ የፓርላማ አባል መሆን ይገባዋል። ይሄ መመዘኛ ለማ መገርሳ፣ ዶክተር አቢይ አህመድ እና ወርቅነህ ገበየሁን በመጀመሪያው ዙር ከጨዋታ ውጭ ያወጣል። ስለዚህ የለማም ሆነ የዶክተር አቢይ ጠቅላይ መሆን እንደማይችሉ የተረጋገጠ ነው።

በሌላ በኩል ደመቀ መኮንን፣ አባዱላ ገመዳ፣ ደብረፂዬንና አዲሱን የደኢህዴን ሊቀመንበር ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፋ ይሆናል። በመሆኑም የትግራይ ነፃ አውጪ ክንፍ የሆነው የፀጥታና ስለላ መዋቅር ሕገ መንግስቱ ሳይሸራረፍ ይተግበር ካለ ጠቅላዩ ደብረፂዬን ሊሆን ይችላል። ተጠቅላዬቹ ደመቀ፣ አባዱላ እና አዲሱን የደኢህዴን ሊቀመንበር  ሊሆኑ ይችላሉ።

የራሴን ግምት አስቀምጬ ለመሄድ ያህል የስለላ እና የፀጥታ መዋቅሩ ለደመቀ መኮንን 60 በመቶ፣ ለአባዱላ 40 በመቶ በመስጠት የደሜክስን ተጠቅላይነት የሚያፀና ይመስለኛል። እናም ከሐይለማርያም ተስተካካይ ሰው በዙፋኑ ላይ እናገኛለን።

እዚህ ላይ የትግራይ ነፃ አውጪ ክንፍ የሆነው የፀጥታና ስለላ መዋቅር በሚፈልገው የህገ መንግስት ማእቀፍ የሚዘልቅ ከሆነ ስለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርም ጥቂት ማውራት ያስፈልጋል። በህገ መንግስቱ መሰረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የፓርላማ አባል መሆን አይጠይቅም። በሌላ አነጋገር ም/ ጠ/ ሚኒስትሩ የፓርላማ አባል መሆን አይጠበቅበትም። እናም ለም/ጠ/ ሚኒስትርነት ህውሓት ወይዘሪት ፈትለወርቅ ( ሞንጆሪኖ)፣ ኦህዴድ ዶክተር አቢይ ሊያቀርቡ ይችላሉ። በእኔ ግምት ወቅቱ ከምንግዜውም በላይ ለትግራይ ነፃ አውጪ ወሳኝ በመሆኑ ወይዘሪት ፈትለወርቅ የመመደብ እድሏ ሰፊ ነው። በሌላ በኩል ዶክተር አቢይን ከስሩ ነቅለው በውሃ ላይ የሚንሳፈፍ ደረቅ ኩበት ማድረጉ የበለጠ የሚጠቅማቸው ከሆነ ምክትል ተጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ ይመድቡታል። በመሆኑም የምክትልነት ጨዋታው ( game theory) የሚሆነው ደመቀ መኮንንን በምትጠቀልለው ሞንጆሪኖ እና ተጠቅላዪ ዶክተር አቢይ መካከል ይሆናል።

የሕውሓት/ ኢህአዴግ ድርጅታዊ ህገ ደንብ

በህውሓት/ ኢህአዴግ ህገ ደንብ መሰረት 180 አባላት ያሉት ( ከእያንዳንዱ 45) የኢህአዴግ ምክርቤት የድርጅቱን ሊቀመንበር በሚስጥር በሚሰጥ ድምፅ ይመርጣል። በድምፅ አሰጣጡ ላይ 180 የምክር ቤት አባላት እኩል ድምፅ አላቸው። ምንም እንኳን ከ3ሚሊዬን አባል እና ከ40 ሚሊዬን በላይ ህዝብ ወክያለሁ የሚለው ኦህዴድ ከግማሽ ሚሊዬን በታች እና ከ5 ሚሊዬን በታች ወክያለሁ የሚለው ህውሃት እኩል ድምፅ መያዛቸው ሊያነጋግር ቢችልም።

በህገ ደንቡ መሰረት አራቱም የዘውጌ ድርጅቶች የኢህአዴግ ሊቀመንበር እና ምክትል አጩ የማቅረብ መብት አላቸው። ለሊቀመንበርነት የሚወዳደሩት የብሔር ድርጅቶቹ ሊቀ መናብርት ይሆናሉ። እዚህ ላይ በህገ ደንቡ ሊቀመንበሩ የድርጅቱ የበላይ አስፈፃሚ መሆኑን ቢገልፅም በመንግስት ስልጣን ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል የሚል በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለም። ለነገሩ ፓርቲው እንደ አቶ መለስ የመንግስት ዘላለማዊነትን ካልተላበሰ በስተቀር ሊያስቀምጥ አይችልም። ነገር ግን ድርጅት መንግስትን የሚመራ እንደመሆኑ መጠን ፓርቲው በውድም ይሁን በግድ ስልጣኑን የተቆናጠጠ በመሆኑ የፓርቲው ሊቀመንበር የመንግስት የበላይ ሆኖ መቀመጡ ተመራጭ ይሆናል።

እናም በዚህ ስሌት መሰረት ከወዲሁ ግምቴን ለማስቀመጥ ህውሓት “ለሊቀመንበርነት እንዲወዳደር የማቀርበው እጩ የለኝም” ይላል። ደብረጲዬንን ከትግራይ አምጥቶ ማወዳደር ከባድ ስለሚሆንበት። ፌዴራሉን በስውር ለመምራት ደብሪፅን ማምጣት አደጋ ይኖረዋል። ብአዴን በሊቀመንበርነት ደመቀ መኮንን እጩ እንዲሆን ያቀርባል። ኦህዴድ ለድርጅት ሊቀመንበርነት በእጩነት የሚያቀርበው የሚኖር አይመስለኝም። ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ ቢመረጥ እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ስለማይችል የፓርቲው ቁንጮ መሆን የሚፈይድለት ነገር የለም። የደቡብ ድርጅቱ ደኢህዴግ አዲሱ ሊቀመንበሩን ለኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እጩ አድርጐ ሊያቀርብ ይችላል። የደኢህዴኑ ሊቀመንበር የፓርላማ አባል ከሆነ ከደመቀ መኮንን ጋር የሚገጥመው ለድርጅት ሊቀመንበርነት ብቻ ሳይሆን ለተጠቅላይነትም ጭምር ይሆናል። እናም የትግራይ ነፃ አውጪ ሙሉ ድጋፍ ያለው ደመቀ መኮንን በተጠቅላይነት አራት ኪሎ ይሰጠዋል።

እና ምን ይጠበስ?

አንዳንድ ሰዎች የቅርብ ወዳጆቼን ጨምሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ማጥፋት እንደማያስፈልግ ሲገልጡ እሰማለሁ። የትግራይ ነፃ አውጪ በሰጠን አጀንዳ ላይ የተጠመድን አድርገው ይወስዱታል። በመሰረቱ በዚህ አስተያየት አልስማማም።

በመጀመሪያ ደረጃ የትግራይ ነፃ አውጪ የገባበት ሁኔታ ቀውስ እንጂ ስኬት አይደለም። የቀውሱ መሰረታዊ ምንጭም የኢትዬጲያ ህዝብ እምቢተኝነት የወለደው እንጂ አገዛዙ የመለወጥ ፍላጐት ስላለው አይደለም። በሕዝብ አመፅ ምክንያት የትግራይ ነፃ አውጪ እየተፍረከረከ፣ የአመራር ሽኩቻው በግልፅ እየታየ ትኩረት አንስጠው ማለት አያስኬድም።አይደለም የአገሬው ሰው ምእራባውያን፣ አለም አቀፍ ተቋማት እና ሚዲያው በትግራይ ነፃ አውጪ ውስጥ የተፈጠረውን የስልጣን ፍጥጫ በአንክሮት እየተከታተሉ ስጋታቸውን በሚገልፁበት ሁኔታ የስርአት ለውጥ ፈላጊዎች ትኩረት ካልሰጠነው የለውጥ ግንዛቤያችንን መፈተሽ ይኖርብናል። ይሄን ማስታወሻ እየፃፍኩ በኢትዬጲያ የአሜሪካን ኤምባሲና አምባሳደር የአቶ ኃይለማርያም ከስልጣን መውረድ ጋር ተያይዞ ይፋ ያደረጉት ማስጠንቀቂያና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ያወጡት መግለጫ በትዝታዬ መጥቶ ነበር። የስርአት ለውጥ ፈላጊውም ሆነ የሚዲያ ተቋማት እንዴት ተሯሩጠው እንደተቀባበሉት ጭው አለብኝ። በብዙ ሰዎች ትንተና ውስጥም ይህ በተደጋጋሚ የሚጠቀስና በእያንዳንዳችን አእምሮ ውስጥ የሚንገዋለል ነው።

በሁለተኛ ደረጃ ደጋግሜ እንደገለፅኩት ትናንሽ ለውጦች ትላልቅ ለውጦችን ይጋብዛሉ። ለነገሩ በትግራይ ነፃ አውጪ ውስጥ የሚኖርን የስልጣን ሽኩቻ እንደ ትንሽ ለውጥ ሊወሰድ ይገባል ወይ የሚለውም መጠየቅ ይኖርበታል። የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት የፋሺስት እና አፓርታይድ ድቃይ በመሆኑ በጣም አደገኛ ነው። ይሄ አደገኛ ስርአት በተነሳበት የሕዝብ ጥያቄ ውስጣዊ ህይወቱ ውስጥ ያጋጠመው የአመራር መፍረክረክ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። እነሱ ሲወድቁ እኛንም ይዘው እንዳይወድቁ ፣ ሽብርና የእርስ በርስ እልቂት እንዳይፈጠር በቅርበት መከታተል ያስፈልጋል። ለማንም ግልጥ እንደሆነው ይሄ ፋሽስታዊ አገዛዝ እስከአሁን ለግፍና ለጭፍጨፋ አዲስ ባይሆንም ከኢትዬጲያ ህዝብ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተቆራረጠበት እና እርስ በራስ መበላላት የጀመረበት ነው። ይሄ በአግባቡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ይሄን ማድረግ ዋናውን ትግል ያግዘዋል እንጂ የሚያዘናጋው አይሆንም። ይልቁንስ በትግራይ ነፃ አውጪ እና ተላላኪዎቹ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል ለመሰረታዊ ለውጡ በአቀጣጣይነት ሊታይ የሚችል ነው። ” የጉልቻ ለውጥ” ብቻ ተደርጐ መወሰድ የለበትም። እንደዚህ ማሰብ ተራራ የሚያክል ስህተት ለመስራት እንደመዘጋጀት ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።

በሶስተኛ ደረጃ በስርአት ለውጥ ፈላጊው ዘንድ የሚታዩ የተሳሳቱ ዝንባሌዎችን ነቅሶ በማውጣት ለመታገል ያግዛል። ይሄ ወቅት ዘረኝነት እና ፋሺዝም አብረው የቆሙበት የሞትና የሽረት ዘመን ነው። የዘረኝነት ፓለቲካ በአገዛዙ ውስጥ ብቻ አይደለም። ተቃዋሚ ሀይሉም ጋር የDNA ፓለቲካ ስር እየሰደደ ሄዷል። እንደዚህ ባለ አደገኛና ደካማ አቋም ምክንያት አመዳዩን አለላ ለማስመሰል ጥረት እየተደረገ ነው። እከሌ በሕዝብ ተወዳጅ ስለሆነ በጠቅላይ/ ተጠቅላይነት ካላየሁት ሞቼ እገኛለሁ የሚሉ አደገኛ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው። ሌሎች ድብቅ ፍላጐት ያላቸው ደግሞ የሕዝቡን ልቦና በማዳመጥ እነሱ ወደሚፈልጉት ለማሽከርከር ያለ የሌለ ጉልበታቸውን በመጠቀም ላይ ናቸው። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ለማ መገርሳ እና ዶክተር አቢይን ወደ ፌዴራል ተጠቅላይነት እንዲሄዱ የሚደረገው ግፊት ነው።

በእኔ እምነት በለማ እና አቢይ ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ከስራቸው በመንቀል አስብቶ የማረድ ነው። እርግጥም ከአፈራቸው ላይ ስራቸውን መንቀል እንዳያብቡ ያደርጋል።ለማና አቢይ ለመካከለኛ ጊዜ የኦሮሚያን የፓለቲካና የድርጅት ስራ በበላይነት መምራት ይኖርባቸዋል። እስከ ሶስት ሚሊዬን ይጠጋል የተባለውን የኦህዴድ አባልና ቄሮን በአዲሱ አስተሳሰባቸው ኢንዶክትሬት ማድረግ ይኖርባቸዋል። በመንግስት የስራ አመራርና የካድሬ ስልጠና ማእከላት ” ኢትዬጲያዊነት ሱስ መሆኑን፣ የብሔር ጭቆና የሚባል ተረት ተረት መሆኑን፣ የኦሮሞ ጀግኖች ኢትዬጲያ አገራቸውን ለማቆየት ያደረጉትን ተጋድሎ፣ ኢትዬጲያዊነት እንደ ጉልት ማንም ሲፈልገው የሚያቋቁመው እና የሚበትነው እንዳልሆነ፣ መታወቂያ ላይ ብሔር መፃፍ ያስቆሙበትን ምክንያት፣ የኦሮሞ ህዝብ ወርቃማ እሴቶችን…ወዘተ” የሚያስተምሩበት ካሪኩለም በመቅረፅ ማስተማር ይኖርባቸዋል። ሚሊዬን ለማዎችና አቢዬች መፈጠር ይኖርባቸዋል። የትምህርት ቤት ካሪኩለሞችን በእነሱ አዲስ ተራማጅ አስተሳሰብ መቃኘት የቅድሚያ ስራቸው ሊሆን ይገባል።

የለማ ቡድን አባላት ከላይ የተጠቀሰውን እያደረጉ የአገሪቱን ሕገ መንግስት ወደ ፕሬዝዳንታዊ ስርአት ( የአንድ ሰው አንድ ድምፅ) የሚቀየርበት ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርባቸዋል። በዚህ ዙሪያ የፕሮፌሰር መረራ ፓርቲ እና የሌሎች ድርጅቶች ድጋፍ ስለሚያገኙ ትግሉ አስቸጋሪ ላይሆን ይችላል።የለማ ቡድን ይሄን ማድረግ ከቻለ በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ ዘወትር የሚታወስ ደማቅ ታሪክ ይሰራል። የኢትዬጲያ አምላክ ይርዳቸው።

ሁለቱ የትግሬ ጋዜጠኞች በትላንት ፕሮግራማቸው እንዲህ አሉ!

Standard

ዮናስ~ “የኢትዮፒካሊንክ ፕሮግራማችን ተጀምሯል…ምን አዲስ ነገር አለ?”

ብርሀነ ንጉሴ ~ “ያው ደስ የሚለው ነገር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታውጇል….”

በ110 ሚሊየን ህዝብ ላይ የተጣለ አስፈሪ አዋጅ “ደስ የሚል ነገር” ነው ብሎ መናገር ምን አይነት ስብዕና ቢሆን ነው?